Pair of Vintage Old School Fru
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

እውነተኛ ሃይማኖት


✍አዘጋጅ: አቡ አሚና ቢላል ፊሊፕስ
ተርጔሚ: ጀማል ሙኽታር

ክፍል 2 Iqra
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የውሸተኛ ሃይማኖት መልእክት

በአለም ላይ ብዙ የእምነት ቡድኖች ፣ ሃይማኖቶች ፣ ፍልስፍናዎችና ንቅናቄዎች ይገኛሉ። ሁሉም ትክክለኛው መንገድ የኔ ነው ወይም ወደ አሏህ የሚወስድ ብቸኛው መንገድ የኔ ነው ብለው ይናገራሉ። እናም አንድ ሰው የትኛው ትክክለኛ እንደሆነ ወይም ሁሉም ትክክለኞች እንደሆኑ ለይቶ ማወቅ እንዴት ይችላል? መልሱን ማግኘት የሚቻልበት ዘዴ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ መንገድ ጥሪ የሚያደርጉበትን ማእከላዊ የአምልኮት ዒላማ ለይቶ በማውጣት ነው። ሐሰተኛ ሀይማኖቶች ሁሉ አሏህን አስመልክቶ አንድ የጋራ ግንዛቤ አላቸው። ሰዎች ሁሉ አማልክት ናቸው፤ ወይም የተለያዩ ሰዎች አሏህ ናቸው፤ ወይም ደግሞ ተፈጥሮ አሏህ ነው ብለው ይላሉ።

ከዚህም በመነሳት የሐሰተኛ ሃይማኖት መሠረታዊ መልእክት አሏህ በራሱ ፉጡራን ተመስሎ ሊመለክ ይችላል የሚል ነው። ሐሰተኛ ሃይማኖት ፍጥረትን ወይም አንድን የፍጥረት ገጽታ አምላክ ነው ብሎ በመሰየም የሰው ልጅ ፍጥረትን እንዲያመልክ ጥሪ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል ነብዩ ኢሳ/እየሱስ(ዐ.ሰ) ተከታዮቻቸው አሏህን እንዲያመልኩ የጋበዙ ሲሆን የእየሱስ(ዐ.ሰ) ተከታዮችነን ባዮች ግን ኢየሱስ ራሳቸው አሏህ ናቸው በማለት ሕዝቡ ኢየሱስን እንዲያመልክ ይሰብካሉ። ቡድሃ አያሌ ሰብአዊ ይዘት ያላቸው መርሆወችን ወደ ሕንድ ያስገባ የተሐድሶ አራማጅ ነበር። አምላክ ነኝ አላለም ወይም የአምልኮታቸው ዒላማ የመሆን ሐሳብ ለተከታዮቹ አላቀረበም ነበር። ነገር ግን ዛሬ ከሕንድ ውጭ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቡድሂስቶች ቡድሀን አምላክ አድርገው በመያዝ በነሱ ግምት በርሱ አምሳል በተቀረጹ ምስሎች ላይ ተደፍተው ይሰግዳሉ።

አምልኮው ዒላማ ያደረገውን ነገር ለይቶ ማውጣት የሚለውን መርሕ በመጠቀም ፣ ሐሰተኛ ሃይማኖት በጣም ግልጽና የሥረ-መሠረቱ ሰው ሰራሽ ተፈጥሮም ገሃድ ይሆናል። አሏህ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ብሏል፦

=<({ሱራ ዩሱፍ 12:40})>=


{40} ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ አምላክ ብላችሁ የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትገዙም፤ አሏህ በርሷ ምንም ማስረጃ አላወረደም፤ ፍርዱ የአሏህ እንጂ የሌላ አይደለም፤ እርሱን እንጂ ሌላን እንዳትገዙ አዟል፤ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው። ግን አብዛኛወቹ ሰዎች አያውቁም።

ሁሉም ሃይማኖቶች መልካም ነገሮችን ያስተምራሉና አንዱን ብንከተል ምን ያመጣል የሚል ክርክር ሊነሳ ይችላል። መልሱ ሐሰተኛ ሃይማኖቶች ሁሉ የፍጡር አምልኮ የሆነውን ከሁሉም እጅግ ከባዱን ጥፋት ነው የሚያስተምሩት የሚል ይሆናል። የፍጡር አምልኮ የሰው ልጅ ተፈጥሮ መሰረታዊ ዓላማ የሚፃረር በመሆኑ በሰው ልጅ ሊፈጸም የሚችል እጅግ የከፋና ከሁሉም በላይ ከባዱ ሀጢያት ነው። ቁርአን ውስጥ በግልጽ እንደተጠቀሰው ሁሉም የሰው ልጅ የተፈጠረው አሏህን ብቻ ለመገዛት ነው።

=<({ሱራ አል-ዛሪያት 51:56})>=


{56} ጅንንም ሰውንም አልፈጠርኳቸውም፤ እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጅ።

ስለ ሆነም የጣዖታዊነት ሥረ-መሰረት በሆነው ሽርክ ላይ ሆኖ የሞተ ሰው በወዲያኛው ሕይወት ዕድሉን ዘግቷል። አሏህ የመጨረሻ በሆነው ወሕዩ(Al Quran) ውስጥ እንዲህ ይላል፦

=<({¯ሱራ አል-ማኢዳህ 4:48¯})>=


{48} አሏህ በርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፤ ከዚህ ውጭ ላለው ለሚሻ ሰው ይምራል።

የኢስላም ዓለም አቀፋዊነት

የሐሰተኛ ሐይማኖት ውጤቶች እጅግ አደገኛ ከሆኑ ዘንዳ ፣ እውነተኛው የአሏህ ሃይማኖት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊረዱትና ሊጨብጡት የሚቻል ሁለንተናዊ የሆነ ሃይማኖት ነው። አማኙ ጀነት እንዲገባ እንደ ጥምቀት እና አዳኝ ነው ብሎ በሰው ማመን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ሊኖሩ አይችሉም። ራስን ለአሏህ ፈቃድ ማስገዛት በሚለው የኢስላም ማእከላዊ መርህ እና ትርጔሜ ላይ ነው። የኢስላም ሁለንተናዊነት መሠረት ያረፈው የሰው ልጅ አሏህ አንድና ከፍጡራኑ ፈጽፅሞ የተለየ መሆኑን ለመገንዘብ በቅቶ ራሱን ለአሏህ ፍቃድ ባስገዛ ጊዜ በአካልና በመንፈስ ሙስሊም ሆኖ ለጀነት ብቁ ይሆናል። በዚህ መሠረትም በማንኛውም ጊዜ በጣም ሩቅ በሆነ የአለም ክፍል የሚኖር ማንኛውም ሰው የፍጡር አምልኮን ውድቅ አድርጐ ወደ አንድ አሏህ በመመለስ ብቻ የአሏህ ሃይማኖት የሆነው የኢስላም ተከታይ ሙስሊም መሆን ይችላል። ይሁን እንጂ አሏህን አውቆ መቀበልና ራስን ለርሱ ፈቃድ ማስገዛት፤ ጥሩውን ከመጥፎው ለይቶ መምረጥን የሚጠይቅና እንዲህ ዓይነቱ ምርጫም ሃላፊነትን እና ተጠያቂነትን የሚያመለክት መሆኑን ልብ ማለት ይገባል። የሰው ልጅ በምርጫው ውጤት ተጠያቂ ነው። ስለዚህ በጐ ሥራ በመሥራት እና ክፍውን ማስወገድ ያስፈልጋል። የመጨረሻው ከፍተኛ በጐ ተግባር ደግሞ አሏህን ብቻ መገዛት ሲሆን የመጨረሻው ከባድ እና ክፉ ሥራ ደግሞ ፍጡራንን ከአሏህ ጋር በማጋራት ወይም በአሏህ ፈንታ ሌላን ማምለክ ነው። ይህ እውነታ በመጨረሻው መለኮታዊ መልእክት <<ወሕይ>> ውስጥ እንደሚከተለው ተገልጿል፦

=<([ሱራ አል-በቀራ 2:62])>=


{62} እነዚያ ያመኑ፤ እነዚያ ይሁዳዊያኖችም ፣ ክርስቲያኖችም ፣ ሳቢያኖችም ከነርሱ መካከል በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመኑ መልካም ሥራም የሰሩ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳ አላቸው፤ በነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም ፣ እነርሱም አያዝኑም።

=<({ሱራ አል-ማኢዳ 5:66})>=


{66} እነሱም ተውራትንና ኢንጂልን፥ ከጌታቸው ወደነሱ የተወረደውን መጽሐፍ ባወቁና ባረጋገጡ ኖሮ ከበላያቸው እና ከእግሮቻቸው ስር በተመገቡ ነበር። ከነሱ መካከል ትክክለኛና ሚዛናዊዎች አሉ። ነገር ግን አብዛሃኛዎቹ ቅጥ ያለፈ ሃጢያትን ይሰራሉ።

አሏህን ማወቅ

ሰዎች አሏህን ለመገዛት ሃላፊነት ይሰማቸው ዘንድ ሁሉም አሏህን የማወቅ ብቃት ሊኖረው ይገባል። የሰው ልጆች በሙሉ አሏህን የማወቅ ተፈጥሯዊ ግንዛቤ እውስጣቸው የተተከለ መሆኑንና አብረውት የተፈጠሩ መሠረታዊ ባህሪያቸው መሆኑን የመጨረሻው መኮታዊ መልእክት(ወሕይ) ያስተምራል።

ሱራ አል-አዕራፍ አንቀጽ 172-173 ውስጥ አሏህ አዳምን ሲፈጥር የአዳም ዝርዮች ወደ ቁሳዊው አለም ከመምጣታቸው በፊት ወደ መኖር እንዲመጡ አድርጐ «ጌታችሁ አይደለሁምን? በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ ፣ ጌታችን ነህ፥ መሰከርን አሉ፤» በማለት ቃልኪዳናቸውን የወሰደ መሆኑን ገልጿል። ከዚያም በመላው የሰው ልጅ እሱ ፈጣሪያቸውና ሊገዙት የሚገባ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ለምን እንዳደረገ አሏህ አብራርቷል። እንዲህ በማለት:- «በትንሳኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፥» ይህም አንተ አሏህ አምላካችን ስለመሆንህ ምንም ሐሳብ አልነበረንም ፣ አንተን ብቻ መገዛት እንደነበረብን ማንም አልነገረንም እንዳይሉ ነው ማለት ነው። አሏህ ማብራሪያውን በመቀጠል እንዲህ ይላል:- «ጣዖታትን ያጋሩት ከኛ በፊት የነበሩት አባቶቻችን ብቻ ናቸው፤ እኛም ከነሱ በኋላ የኾን ዘሮች ነበርን፤ አጥፊዎቹ በሠሩት ታጠፋናለህን እንዳትሉ አስመሰከርናችሁ።»


  • ስለዚህ እያንዳንዱ ሕፃን በአሏህ የማመን ተፈጥሮና እሱን ብቻ የማምለክ ዝንባሌ አብሮት ይወለዳል። ይህ ተፈጥሮ በአረብኛ ፊጥራህ ተብሎ ይጠራል።


  • ሕፃኑ ለብቻው ቢተው ኖሮ በራሱ መንገድ አሏህን ይገዛ ነበር። ዳሩ ግን ሕፃናት ሁሉ በሚታዩም ሆነ በማይታዩ ነገሮች በአካባቢያቸው ተጽእኖ ሥር ይወድቃሉ። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) «አሏህ ባሮቼን የፈጠርኴቸው በትክክለኛው ሃይማኖት ላይ ነው፤ ነገር ግን ሰይጣኖች ያጠሟቸዋል ብሏል ማለታቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እያንዳንዱ ሕፃን "በፊጥራ" ሁኔታ ላይ ሆኖ ይወለዳል፤ ይሁዳዊ ፣ ክርስቲያን ወይም ዞራስተሪያን (እሳት አምላኪ) የሚያደርጉት ወላጆቹ ናቸው፤.....ብለዋል።»

    {ቡኻሪና በሙስሊም}

    ሕፃኑ ልክ አሏህ በተፈጥሮ ውስጥ ባኖራቸው ፊዚካል ሕግጋት ተገዥ እንደሆነ ሁሉ ነፍሱም አሏህ ጌታዋና ፈጣሪዋ ለመሆኑ እውነታ በተፈጥሮዋ ተገዥ ትሆናለች። ነገር ግን የሕፃኑ ወላጆች የራሳቸውን መንገድ እንዲከተል ለማድረግ የሚሞክሩ ሲሆን ሕፃኑ በመጀመሪያዎቹ የእድሜ ዘመኑ የወላጆቹን ፈቃድ ለመቇቇምም ሆነ ለመቃወም አቅም የለውም። በዚህ ደረጃ ላይ ሕፃኑ የሚከተለው ሃይማኖት የወግ ልማዱና የአስተዳደግ አካባቢው አይነት ነው። አሏህም በዚህ ደረጃ ላይ ሕፃኑን በዚህ ሃይማኖት ምክኒያት ተጠያቂ አያደርገውም።

    ከልደት እስከ ሞት ባለው የሕዝቦች ሕይወት ውስጥ አንድ እውነተኛ አምላክ አሏህ ብቻ መሆኑ ግልጽ እስኪሆንላቸው ድረስ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶችና ታአምራት በምድር ውስጥና በራሳቸው ነፍስ ውስጥም ይገለጹላቸዋል። ሰዎች ከራሳቸው ጋር እውነተኛና ታማኞች ሆነው የሐሰት አማልክቶቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው አሏህን ቢፈልጉ....መንገዱ ቀላል ይሆንላቸዋል። የአሏህን ምልክትና ተአምራቱን እምቢ ብለው ውድቅ ማድረጉን ቢቀጥሉበትና ፍጡራንን በመገዛቱ ተግባር ቢገፉ መንገዱ የበለጠ አስቸጋሪና የማይወጡት ይሆንባቸዋል። ለምሳሌ ያህል ደቡብ አሜሪካ ብራዚል ውስጥ ባለው የአማዞን ደቡብ ምስራቃዊ ጫካ ውስጥ አንዱ ኋላቀር ጐሳ «እስክዎች» ለተባለና የፍጡራን ሁሉ አምላክ ለሚወክል ዋነኛ ጣዖት መኖሪያ አዲስ ጐጆ ሰሩ፤ በሚቀጥለው ቀን አንድ ወጣት አምላክ ተብየውን እጅ ለመንሳት ወደ ጐጆው ይገባል። ወጣቱ ፈጣሪውና ሲሳይ ሰጭው እንደሆነ ትምህርት በተሰጠው መሠረት ለጣዖቱ በመስገድ ላይ እያለ እርጅና የተጫጫነው በቆዳ በሽታ የተጠቃና በቁንጫ የተወረረ ውሻ ወደ ጐጆው ገባ። ወጣቱ ሰው ምን ያደርግ ይሆን ብሎ ሲጠብቅ ውሻው የኋላ እግሩን ያነሳና በጣዖቱ ላይ ሲሸና ይመለከታል። ስሜቱ ክፉኛ የተነካው ወጣት ውሻውን ከቤተ-መቅደሱ በቁጣ አባረረው። ቁጣው ሲበርድለት ግን ጣዖቱ የፍጥረት አለም ጌታ ሊሆን እንደማይችል ተገነዘበና አሏህ ሌላ ቦታ መሆን አለበት አለ። ወጣቱ አሁን ግንዛቤውን ተጠቅሞ አሏህን መፈለግ ወይም ታማኝነት በሌለው ሁኔታ የጐሳውን የተሳሳተ እምነት በጭፍኑ ተከትሎ የመጓዝ አማራጭ ቀርቦለታል። ነገሩ እንግዳ ሆኖ ቢታየውም የተከሰተው ነገር ለዚያ ወጣት ሰው ከአሏህ የሆነ ምልክት ነው። እርሱ ሲያመልክ የነበረው ነገር ውሸት መሆኑን የሚያሳይ መለኮታዊ መመሪያ እውስጡ ያቀፈ ምልክት ነው።

    ቀደም ሲል እንደተገለፀው ለሁሉም ህዝቦችና ለሁሉም ጐሳዎች የሰው ልጅ በአሏህ ያለውን ተፈጥራዊ እምነትና እርሱን ብቻ የመገዛት አብሮት የተፈጠረ ዝንባሌውን ለማጠናከርና በአሏህ ተገልፀው በየእለቱ ከሚስተዋሉ መምልክቶች ውስጥ የሚንፀባረቀውን መለኮታዊ እውነታ ለማጐልበት ነቢያት ተልከዋል። በአብዛኛዎቹ ሁኔታ ከነቢዮቹ ትምህርቶች ውስጥ አብዙዋቹ የተበረዙ ቢሆንም ቅሉ ትክክለኛውንና የተሳሳተውን ለይቶ ማመልከት የሚያስችሉ በከፊል ተርፈዋል። ለአብነት ያህል የተውራት አስርቱ ትእዛዛት ወንጌሎች ውስጥ የሚገኙ የነርሱ ማጠናከሪያዎች የነፍስ ግድያ የስርቆትና የዝሙት ወንጀል መቅጫ ህጐችን በአብዛኞቹ ህብረተሰቦች ዘንድ መኖር መጥቀስ ይቻላል።

    ከዚህም በመነሳት እያንዳንዷ ነፍስ በአሏህ ማመንና ራስን ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ፈቃድ ማስገዛት የሆነውን የእስልምና ሃይማኖትን መቀበል ሃላፊነትና ግዴታ አለባት።

    እሱ በመራን ትክክለኛው መንገድ ላይ እንዲያጽናናን ከሱ የሆነ በረከት ይሰጠን ዘንድ ሃያሉ አሏህን እንለምናለን፤ እሱ በእርግጥ ከሁሉም በላይ ቸርና ርህሩህ ነው። ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአሏህ ይሁን። የአሏህ ሰላምና በረካ በነብዩ ሙሐመድና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በባልደረቦቻቸውና በቅንነት ፈለጋቸውን በተከተሉ ሁሉ ላይ ይሁን።


    Iqra
    Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
    Iqra

    362

    የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
    free book gift

    Download Islamic Books
    ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

    Important Web Links


    free book gift

    free book gift

    free book gift

    ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

    Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ